“የፋሽሰቱ ቡድን ቀይ-ውሸት በትግራይ ሰራዊት በማያዳግም ምቱ!-ዕርቃኑ አስቀረው”!!

ፋሽስት ቡድኑ መንበረ ስልጣኑ በተቆናጠጠበት ወቅት የሰላምና እውነተኛ የለውጥ ኃዋርያ መስሎ፣ ቅጥፈት በተሞላበት አኳኃን በአጉል ተስፋ የኢትዮጵያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ በማጭበርበርና በማደናገር የኖቤል ሰላም ሽልማት አግኝቷል። ነገር ግን የፋሽስት ቡድን አብይ አሕመድና ጭፍራዎቹ፣ ፀረ ሰላም ብቻ ሳይሆኑ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ የፈፀሙ ወንጀለኞች መሆናቸው የተለያዩ ሃገራት መሪዎች፣ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ የሰብኣዊ መብት ተማጓች አካላት እንዲሁም በዓለም ተሰሚነት፣ ተደማጭነትና ተነባቢነት ያላቸው ሚድያዎች የቡዱኑን አሰቃቂ ግፎችና “ቀይ ውሸት” በየእለቱ በማጋለጥ ላይ ናቸው።

ባርባራዊ የጀኖሳይድ ግፍ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ ቀይ ውሸት መለያው የሆነው የፋሽስት ቡድኑ በበኩሉ፣ ቀጣፊነት ተረድቶ አንቅሮ ለተፋውን ዓለም ኣቀፍ ማሕበረሰብ ሲያወግዝ ከርሟል። ሰሞኑ ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት /ተመድ ሰብኣዊ ምክር ቤት የጠራው እና በርካታ ሃገራት የሚሳተፉበት ስብሰባ ለማደናቀፍ ላይ ታች በማለት ተጠምዷል። ፋሽስት ቡድኑ ከሸሪኮቹ ጋር ሆኖ ስብሰባ እንዳይካሄድ እየጣረ የሰነበተው፤ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመው ጀኖሳይድ በተለይም ከባለፈው ወር ጀምሮ በሆለካስት መልክ በመላ አገሪቱ በማጎርያ ካምፖች (Concentration camps) አጉሮ በቁማቸው እያሰቃያቸው ያሉት ከ40ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች ሁኔታ፣ እንዲሁም በአጠቃላይ በመላ ሃገሪቱ እየፈፀማቸው ያለው ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው አረመንያዊ ግፎች፣ የተመድ ሰብአዊ ምክር ቤት ዘርዝሮ እራቆቴ እንዲወጣ ያደርጋል በሚል ስጋት የሚይዘውና የሚጨብጠው ጠፍቶት፣ ተደናብሮ የእሪታ ለቅሶ በማሰማት ላይ ይገኛል።

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የፋሽስት ቡድኑ በ2013 ዓ.ም በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀማቸው የጀኖሳይድ ግፎች ለመሸፈን ግራና ቀኝ ቢቅበዘበዝም፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመው አረመንያዊ ግፍ በተመሳሳይ አኳኋን የፈፀመባቸውና እየፈፀመባቸው ያሉት የአፋርና የአማራ አርብቶ አደሮችና አርሶአደሮች፣ ንፁህ ህሊና ያላቸው የከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም በየጦር ሜዳው የተማረኩ የራሱ ታጣቂዎች፣ ከማለዳው ምስክርነታቸው ሰጥተዋል። ንፁህ ህሊና ያላቸው የአማራ ብሄር ተወላጆችም በቀይ ውሸት ተጠምቆ፣ ወደ መቃብሩ እያዘገመ ያለውን የፋሽስት አብይ አሕመድ ቡድን በኮምቦልቻ፣ በደሴና በአንዳንድ የሰሜን ሸዋ ከተሞች የትግራይ ሰራዊት አዉድሞታል ዘረፋ ፈፅሟል በማለት ነጋ ጠባ እያሰራጨው ያለው ውሸት ከእውነት የራቀ መሆኑን በኦንላይን ሚድያ በማጋለጥ ላይ ናቸው።

በከተሞቹ ዙርያ የተካሄዱትና እየተካሄዱት ያሉት አሳዛኝና አሰቃቂ ዘረፋዎችና በደሎች በፋሽስት ቡድኑ ታጣቂዎች በዋነኛነት በፋኖ ስም የሚታወቁ ወረበሎች መሆናቸው እውነተኛ ምስክርነታቸው በመስጠት ላይ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ይሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ እንደሚባል የተባበሩ መንግስታት ድርጅት የፋሽስት አብይ አሕመድ ቅጥረኛ ታጣቂዎች የአማራን ህዝብ ለመታደግ የላካቸውን 18 የጭነት ተሽከርካሪዎች ከተጫኑት መድኃኒት ጋር በጠራራ ፀሃይ ዘርፎው እንደ ወሰዱ ይፋ አድርገዋል።

መንበረ ስልጣኑ ከመጠበቅ ውጪ ለህዝብና ለሃገር ቅንጣት ታክል ደንታና ጥብቅና የሌለውየ ፋሽስት አብይ አሕመድ ቡዱን፣ የትግራይ ሰራዊት በራሱ ፍላጎት የለቀቃቸው አንዳንድ የሰሜን ሸዋ እንዲሁም ኮምቦልቻ እና ደሴ ከተማዎችን በውግያ እንደያዘ አስመስሎ መዋሸቱ ሳያንስ ሰሞኑ ደግሞ በዚሁ ገባሁ፣ ተራራ ያዙኩኝ፣ መንገድ ቆረጥኩኝ፣ ወዘተ በማለት በዋነኛነት በጋሸና ግንባር ድል ተቀዳጅቻለሁኝ ሲል ያለ ምንም ኃፍረት በጠራራ ፀሃይ በአደባባይ ዋሽተዋል። ሃቁ ግን ሌላ ነው። አስገድዶና አወናብዶ በርከት ያለው ገጀራ እና ባዶ እጁን በማስገባት ጭዳ እንዲሆን የፈረደበትን ከ80ሺ በላይ ታጣቂ ሃይሉን በትግራይ ሰራዊት ወደር የለሽ ጀግንነት በጋሸና ግንባር እንዳልነበረ ሆኖ የውኋ ሽታ ሆኖዋል።

በአጠቃላይ የፋሽስት ቡድኑ ቀይ ውሸት እያሽቆለቆለ ያለው የሃገሪቱ ማህበረ ኢኮኖሚ አባብሶ፣ የዋጋ ንረት ጣርያ ደርሶ፣ ህዝቡ በድህነትና ኑሮ ውድነት አረንቋ አስገብቶ፣በቁሙ እንዲሰቃይ ፈርዶበታል። በመሆኑም የፋሽስት አብይ አሕመድ ውድቀት አይቀሬ መሆኑ በውል የተገነዘበው ዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ፣የተለያዩ ተቋማት እና ሃገራትም ተወካዮቻቸው፣ አምባሳደሮቻቸውና ሰራተኞቻቸው ከኢትዮጵያ እንዲወጡ አድርጓል።

በመጨረሻም ፋሽስት አብይ አሕመድ ያለ ምንም ይሉኝታ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሁነኛ መሳርያ አድርጌ እደነፋለሁኝ ያለው ቅጥፈት፣የትግራይ ሰራዊት በየግንባሩ እያደረሰበት ባለው የማያዳግም ምት፣ ያሰራጨው ሃሰተኛ የውዥንብር ማዕበል ራሱን መልሶ እርቃኑን በማስቀረት፣ ቀይ ውሸት ስለመሆኑ ወለል ብሎ በመታየት ላይ ነው።ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝቦች የፋሽስት ቡድኑ ቀይ ውሸት በማጋለጥና እድሜው ለማሳጠር የምትረባረቡበት ወቅት አሁን መሆኑ ተረድታቹሁ የድርሻቹ ልትወጡ ይገባል።

ህልውናችንና ደህንነታችን በፈርጣማው ክንዳችን!
ትግራይ ታሸንፋለች!
የትግራይ ኮሚኒዩኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
ታሕሳስ 8/2014 ዓ.ም
መቐለ

Share.

Leave A Reply